የፓርቲው አባል ለመሆን መመዘኛዎች
የብልጽግና ፓርቲ አባል ለመሆን ከዚህ በታች የተመለከቱትን መመዘኛዎች የሚያሟላ ማንኛውም
ኢትዮጵያዊ ዜጋ የፓርቲው አባል መሆን ይችላል።
- የፓርቲውን ፕሮግራምና መተዳደሪያ ደንብ ተቀብሎ
በጽናት ተግባራዊ ለማድረግ ፍቃደኛ የሆነ፤
- መልካም ሥነ-ምግባር ያለውና በኅብረተሰቡ ውስጥ
ተቀባይነት ያለው፤
- በኅብረ ብሔራዊነት እና በሀገራዊ አንድነት ላይ ጽኑ
አቋም ያለውና ዋልታ-ረገጥ አመለካከትና ተግባሮችን
በጽናት የሚታገል፤
- ዜጎችንና ሕዝቦችን በእኩልነት የሚያገለግል፣ የሕዝብ
ጥቅምን የሚያስቀድም፣ከሙስናና ብልሹ አሠራሮች ራሱን
ያራቀና ሌሎችንም የሚታገል፤
- የፓርቲውን ዕሴቶችና ዓላማዎችን ተቀብሎ የተሰጠውን
ኃላፊነት ለመወጣት ቁርጠኛ የሆነ፤
- ወርኃዊ የአባልነት ክፍያ ለመክፈል ፍቃደኛ የሆነ፤
- እድሜ 18 ዓመት እና ከዚያ በላይ የሆነ፤
- የሌላ ፖለቲካ ፓርቲ አባል ያልሆነ፤
- የፖለቲካ ፓርቲ አባል የመሆን መብቱ በሕግ ያልተገደበ
ወይም በፍርድ ቤት ውሳኔ ያልተገፈፈ፤
- በዚህ ደንብ በተወሰነው መሠረት የሙከራ ጊዜውን የጨረሰ
የፓርቲው አባል መሆን ይችላል።