ዜና | Oduu | News
በመደመር መንግስት እይታ የዘርፎች እመርታ!" በሚል ርዕስ ለአባላት ሲሰጥ የነበረ ስልጠና ተጠናቀቀ።

በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ለብልፅልግና ፓርቲ አባላት በመደመር መንግስት እይታ የዘርፎች እመርታ!" በሚል ርዕስ ለአባላት ሲሰጥ የነበረ ስልጠና ተጠናቀቀ። የልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰለሞን ስብሃት ስልጠናውን ሲያጠቃልሉ እንደገለፁት የማህበራዊ ፣ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ሀገርን ወደ ከፍታ የማሻገር ህልማችንን በጋራ በመሆን በመፍጠር ፣ በመፍጠን እና በመስፈንጠር የላቁ ድሎችን ማስመዝገብ የሚያስችሉ ፀጋዎች እና አቅሞች መኖራቸውን ገልፀው ከተሞች አዲስ አበባን ጨምሮ በፕላን ባለመመስረታቸው ተግዳሮቶች እንደነበሩ በተለይም የኮሪደር ልማት ከተሜነት ባህልን መገንባት የራሱን ገፅታ እንደፈጠረ ገልፀዋል። የወረዳው ብልፅግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ አይናለም ብርሃኑ በበኩላቸው የገጠር ግብርና ትራንስፎርሜሽን ፣ የከተማ ልማት ፣ የኢንዱስትሪ እና የቱሪዝም ዘርፎች ሀገራዊ መዋቅራዊ ሽግግር ለማምጣት እንዲሁም ለሌሎች ዘርፎች አስቻይ ሁኔታ በመፍጠር ለሀገረ መንግስት ግንባታ ትልቅ አቅም ስለሚፈጥሩ በስልጠናው ልዩ ትኩረት እንደተሰጣቸው ገልፀዋል። ውጥኖቻችንን ከግብ ለማድረስ የእያንዳንዳችን ድርሻ የላቀ መሆኑን አመላክተዋል። በስልጠናው ላይ ለተሳተፋ አባላት በቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ተግባቦት በመፍጠር ስልጠናው ተጠቃሏል።

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 አስተዳደር ህዝባዊ የዉይይት መድረክ ተካሔደ።

በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 አስተዳደር "የጉባ ብስራቶች፤ የመደመር መንግስት ትሩፋቶች" በሚል መሪ ቃል የሕዝባዊ የውይይት መድረክ በዛሬዉ እለት ተካሔዷል። በወረዳዉ በተካሔደው የውይይት መድረክ የሃይማኖት አባቶች፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶችና ሴቶች፣ የንግዱ ማህበረሰብ፣ ባለሀብቶችና ምሁራንን ጨምሮ የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ተወካዮች ተሳታፊ ሆነዋል። የጉባ ብስራቶች የመደመር መንግስት ቱሩፋት በሚል ርዕስ ከዚህ ቀደም በተለያዩ የሕዝብ መድረኮች ላይ ከነዋሪዎቻችን ለተነሱ ጥያቄዎች፣ ቅሬታዎች እና አስተያየቶች በተግባር የተሰጡ ምላሾች፣ እንዲሁም ቀሪ ሥራዎችን አስመልክቶ በወረዳዉ ዋና ስራ አስፈፃሚ በአቶ ደረጄ ፈይሳ በዝርዝር ቀርበው ውይይት ተካሂዶባቸዋል። በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 በተካሔደው የህዝብ የውይይት መድረክ አቶ ገዛኸኝ ዴሲሳ የአዲስ አበባ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዳይሬክተር ፣ወ/ሮ ተስፋነሽ ጋሻው የክፍለ ከተማው ንግድ ፅ/ቤት ሀላፊና የወረዳው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ደረጄ ፈይሳ በጋራ መርተውታል። ባለፉት የለውጥ ዓመታት በከተማችን በተለያዩ የልማት ሥራዎች አስደናቂ ስኬቶች የተመዘገቡት መንግሥትና ሕዝብ አንድ ሆነው በመቀናጀትና በመናበብ ሊፈጽሟቸው በመቻላቸው መሆኑን በውይይቱ ተብራርቷል። በውይይቱ በመንግሥትና በሕዝብ ትብብር የተሰሩ በርካታ ሥራዎችን እና የተመዘገቡ ውጤቶችን ይበልጥ ለማጠናከር፣ እንዲሁም የሕዝብን ተሳትፎ ይበልጥ በሚያረጋግጡ ቀጣይ የጋራ ዕቅዶች ላይ ዳር ማድረስ እንደሚደሚባ መግባባት ተፈጥሯል።

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
የልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 አስተዳደር ስራና ክህሎት ጽ/ቤት በወረዳው ለሚገኙ ለስራ ፈላጊ ወጣቶችና ሴቶች የልል ክህሎት ስልጠና ተሰጠ።

በስልጠናው ላይ ተገኝተው መልእክት ያስተላለፉት የወረዳው ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ኃላፊ ኢ/ር ይትባረክ ብርሃነ ሰልጣኞች የስራ ዕድል ተጠቃሚ ለመሆን ወደ ስራ ከመግባታቸው በፊት በስራ ላይ ማድረግ ባለባቸው ጉዳዮች ላይ እና ስራቸውን በእውቀት እንዲሰሩ ማድረግ ውጤታማነታቸው ላይ ያለው አስተዋፆ ከፍተኛ በመሆኑ ስልጠናውን በአግባቡ መከታተል ይገባቸዋል ብለዋል ግንዛቤ ለመፍጠር እንደሚረዳም ገልጸዋል። የወረዳው ም/ስራ አስፈፃሚና የስራ ክህሎት ፅ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ የክቴ የማታው ስልጠናው ለስራ ውጤታማነት አቅም የሚፈጥርና የሚያግዝ መሆኑና እንዲሁም በሚመርጡት የስራ ዘርፍ ስራውን በእውቀት እንዲሰሩ ከማገዝ አኳያ ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳለውና በቀጣይም ስልጠናውን ወደ ተግባር መቀየር እንዳለባቸው በአፅንኦት ገልፀዋል።

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ በዓል በሰላም እንዲከበር አስተዋጽኦ ላበረከቱ የጸጥታ አካል እና የሰላም ሰራዊት አባላት የምስጋና እና የዕውቅና መርሐ-ግብር ተካሄደ።

በልደታ ክፍለ ከተማ የወረዳ 08 አስተዳደር የመስቀል ደመራና የኢሬቻ በዓል በሰላም እንዲከበር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የጸጥታ መዋቅር አባላትና ለሰላም ሰራዊት አባላት የምስጋና ፕሮግራም የተካሄደ ሲሆን በፕሮግራሙ ላይ የወረዳው የጸጥታ መዋቅር አባላትና የሰላም ሰራዊት አባላት ተገኝተዋል። የልደታ ክ/ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍታለሁ ከፍያለሁ በመልዕክታቸው ሰላምን ለማረጋገጥ የከተማ እና የክፍለ ከተማ እና የወረዳ አመራሮች ፣የፌዴራል እና የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት ፣ደንብ ማስከበር፣ የወረዳው የፀጥታና የሰላም ሰራዊቱ አባላት ፣ ወጣቶች ፣ፎሌዎች የማይተካ ሚና በመጫዎት የመስቀል ደመራና ኢሬቻ በዓል በሰላም እንዲከበር ላበረከታችሁት አስተዋጽኦ ከፍተኛ ምስጋና አቀርባለሁ በማለት በቀጣይ ጊዜም ከተለያዩ የጸጥታ ተቋማት ጋር በቅንጅት በመስራት የከተማውን የክፍለ ከተማውን የወረዳውን ሰላምና ጸጥታ ከምን ግዜም በላይ ሳያሳስበን በታላላቅ ሐገራዊ ፕሮጀክቶች በልማቱ ብቻ ምናተኩርበት አመት እና የኢትዮጵያዊን የከፍታን የምናረጋግጥበት እና ቀጣይ ሐገራዊ ምርጫ በአሸናፊነት የምናጠናቀቅበት ይሆናል በማለት ለተሳታፊዎች በፓርቲና እና በራሳቸው ስም አመስግነዋል። የልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ደረጄ ፈይሳ የመሰቀል ደመራና እሬቻ በዓል መጠናቀቅን አስመልክቶ ነዋሪው እና የጸጥታ ተቋማት ጋር በቅንጅት በመስራት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል ከምንጊዜውም በላይ ላደረገው አስተዋፅኦ ምስጋናቸው ላቅ ያለ እንደሆነ ገልፀዋል። በስተመጨረሻም በተለያየ መንገድ አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት የሰርተፍኬት እውቅና እና ምስጋና ተካሂዷል እንደዚህ አይነት ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ተገልፀዋል። መስከረም 29/2018 ዓ.ም

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
ጠንካራ የፓርቲ ተቋም ለመገንባት የሚያስችል የመልሶ ማደራጀትና የቅድመ ዝግጅት ተግባራት መከናወናቸዉን በሱፐርቪዥን ቡድን ምልከታ ተደርጓል።

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የተቋቋመ የሱፐርቪዥን ቡድን በልደታ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤትና በወረዳ 1,4 እና 06 ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች በመገኘት ሲያካሂድ የቆየውን ሱፐርቪዥን በዛሬው ዕለት በማጠናቀቅ ግብረ መልስ ሰጥቷል። በበጀት አመቱ ጠንካራ የፓርቲ ተቋም ለመገንባት እና የገዥ ትርክት ግንባታን የሚያረጋግጡ የፖለቲካና የአደረጃጀት ዕቅዶች ታቅዶ ወደ ተግባር የተገባ ሲሆን ለዚህ መሳካት የሚያስችሉ የመልሶ ማደራጀት እና የቅድመ ዝግጅት ተግባራት መከናወናቸዉ ይታወቃል። ተግባሩ የተመራበትን አግባብና የተገኙ መልካም ልምዶችን ለማስፋት እና አልቆ ለመፈፀም ክፍተቶችን ለማረም ዓላማ ያደረገ የሱፐርቪዥን ቡድን የፖለቲካና አደረጃጀት ስራዎችን በክፍለ ከተማ፤ በወረዳ፤ በህብረት እና ቤተሰብ ምልከታ አድርጓል። ጠንካራ የፓርቲ ተቋም ለመገንባት የሚያስችል የመልሶ ማደራጀትና የቅድመ ዝግጅት ተግባራት መከናወናቸዉ በግብረ መልስ የተመላከተ ሲሆን በአፈፃፀም ሂደት የተስተዋሉ ክፍተቶችን ፈጥኖ በማረም ጠንካራ የፓርቲ ተቋም ግንባታ ግብ ስኬት ርብርብ ማድረግ እንደሚገባ ተገልጿል። #prosperiry_lideta_branch. #በአዲስ_እይታ_የልደታ_ከፍታ #ጠንካራ_ፓርቲ_ለጠንካራ_መንግስት

image
image
image
image